
” ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ይመስላል ” – ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም መታሰቢያ ፋውንዴሽን 4ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ትላንት እሁድ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል።
ጉባኤው ትኩረቱን ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከተቋቋመበት እና ስራ ከጀመረነት ጌዜ አንስቶ ምን ምን አብይ ጉዳዮችን አከናወነ ? ምን እንቅፋቶች ገጠሙት? ለእንቅፋቶቹስ ምን መፍትሄ ሰጠ የሚለውን ዋና የመወያያ አንጀዳ አድርጎ ነበር።
በዚሁ መድረክ የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ንግግር አድርገዋል።
ዳንኤል (ዶ/ር) ፤ ” ትልቁ ጥያቄ መሆን ያለበት ሰላም እንዴት ይምጣ ? የሚለው ነው ” ብለዋል።
መንግስትም ሲጠየቅ ” ሰላም እፈልጋለሁ፣ ሽማግሌ ልክያለሁ ሞክሬያለሁ፣ ሰላም አጥተናል ሰላም እንዲሆን እመኛለሁ ” ይላል።
ታጣቂ ቡድኖችም ሲጠየቁ ” እኛም ሰላም እንፈልጋለን ተገደን ነው ወደዚህ ነገር ውስጥ የገባነው ” ይላሉ።
ስለዚህ ሁለቱም ሰላምን እንፈልጋለን የሚሉ ወገኖች ናቸው ሰላምን እንዴት እናጸናለን የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኖብናል ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሉ ገልጸዋል።
” ይሄ የሰላም ጥያቄ ለመንግሥት እና ለተፋላሚ ወገኖች ብቻ የሚተው መሆን የለበትም ” ብለዋል።
ተመሳሳይ የሆነ የግጭት ዓውድ ውስጥ ባለፉ ሃገሮች ልምድ መሰረት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚከተሏቸው ስልታዊ እና ተቋማዊ ሂደቶች አሉ እነዚህም የሃገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትህ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
እነዚህ ሁለት መፍትሄዎች ቀደም ብለው ተጀምረው ተግባራዊ እየሆኑ መሆኑን ተናግረው የተዓማኒነት ጥያቄ ግን እየተነሳባቸው መሆኑን አንስተዋል።
” ሂደቱ በተቻለ መጠን ሁሉን አሳታፊና ተዓማኒ እንዲሆን ይፈለጋል፤ ነገር ግን በተዓማኒነታቸው ላይ ጥያቄ ምልክት ተነስቶባቸዋል። ይህ አይነቱ የተዓማኒነት ጥያቄ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የተነሳ ጥያቄ አይደለም ተመሳሳይ ሂደት በተከተሉ ሃገሮች በሙሉ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል ” ሲሉ ገልጸዋል።
” የተዓማኒነት ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ችግር ባይሆንም በቀላሉ የሚታይ ግን አይደለም ነው ” ያሉት።
” አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠመን ችግር ውስብስብነት የተነሳ በየቦታው የምናየው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ነው ” ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ ” ከችግሩ ክብደት አንጻር ላይገርም ይችላል ነገር ግን ብዙ ነገሮች እየመጡ ሲያልፉ አይተናል አሁን ያለውም ችግር ከኢትዮጵያውያኖች አቅም በላይ ነው ብዬ አላስብም ” ብለዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine