ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በተለያዩ መድረኮች ያደረጓቸው ንግግሮች

የፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ትምቢታዊ ንግግር ፟ ነሀሴ 1996

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በነሐሴ 1996 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ማህበር ባዘጋጀው የራዕይ 2020 መድረክ ላይ ኢትዮጵያ ምን ሊገጥማት እንደሚችል፣ ምን ፈተናዎች እንደሚጋረጡባት እና እንዴትስ ከእነዚህ ፈተናዎች ተሻግራ እንደ አገር መቀጠል እንደምትችል ያቀረቡት እጅግ መሳጭና በጥናት ላይ የተመሰረተ፤ ዛሬ ላይ ሆነን ስናደምጠው ደግሞ የሳቸውን አሻግሮ በርቀት የመመልከት እና ባለ ራዕይ ምሁር እንደነበሩ በገሃድ ያሳየ ትንቢታዊ ንግግራቸውን በዚህ ቪዲዮ ላይ ያገኛሉ፡፡ በስማቸው የተቋቋመው ፋውንዴሽን ይህን ታሪካዊ ቪዲዮ ቀድተውና አቆይተው ህዝብ እንዲሰማው ላደረጉ አካላት በጠቅላላ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡