የፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም መታሰቢያ ፋውንዴሽን

የልገሳ መረጃ
(Donation Information)

በኢትዮጵያ

Account Name: Professor Mesfin Woldemariam

Bank of Abyssinia: 58190993

Commercial Bank of Ethiopia: 1000564115405

በአውሮፓ
UBS Savings Account CHF
IBAN CH51 0027 9279 C811 8096 0
Account No. 279 -C8118096 0

በአሜሪካ
Salem Five Bank
Routing Number: 211370558
Account Number: 10001981304

የድርጅቱ አመሠራረት

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የሕይወት ዘመናቸውን ሁሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከድህነትና ከርሃብ አንዲላቀቅ፣ ማሕበራዊ ፍትሕ እንዲያገኝና ሰብዓዊ መብቶቹና ነፃነቱ እንዲከበሩለትና በእኩልነት እንዲኖር ሲታገሉ የኖሩ ሰው ነበሩ። ፕሮፌሰር መስፍን፤ ኢትዮጵያ ከድህነት እና ከእርስ በርስ ግጭት ተላቅቃ፣ ነፃነት የሰፈነባትና ዜጎቿ ከድህነት ተላቅቀው የሚኖሩባት አገር ሆና ለማየት ካላቸው ታላቅ ምኞት የተነሳ እስከ ህልፈታቸው ጊዜ ድረስ ለነኝህ ቁልፍ ነገሮች መሳካት  የበኩላቸውን ሲጥሩ፣ ከአገዛዝ ሥርዓቶቹ ጋር ሲታገሉና ሕዝቡን ሲያስተምሩ የኖሩ ታላቅ ሰው ናቸው።
ፋውንዴሽኑም በግንቦት ወር 2013 በኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ማቋቋሚያ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 የተቀመጡትን መስፈርቶች በማሟላት እንደ አገር ውስጥ የበጎ አድራጊ ድርጅት ተመዝግቦና በቁጥር 5595 የእውቅና ሰርቲፊኬት ተስጥቶት ሕጋዊ ሰውነት አግኝቶ በመንቀሳቀስ ላይ ያለ ተቋም ነው።

የፋውንዴሽኑ መርሆዎች (Principles)፤

ሀ. ሰብዓዊነት
ለ. ሃቀኝነት
ሐ. አለማዳላት (ከአድሎና ከወገንተኝነት መራቅ)
መ. ለእውነትና ለፍትሕ መቆም
ሠ. የሃገርን ብሔራዊ ጥቅም አለማስነካት
ረ. የሰው ልጆች ሁሉ መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በእኩል መከበርና መረጋገጥ

የፋውንዴሽኑ ራዕይ (Vision)፤

የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ፋውንዴሽን ዋነኛ ራዕይ ፕሮፌሰር ሕይወታቸውን ሙሉ ሲጥሩለት የነበረውን ኢትዮጵያን ከድህነት፣ ከርሃብ፤ ከችጋር፤ ከፍትሕ እጦትና ከሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ተላቅቃ የማየት ሕልም እውን እንዲሆን የበኩሉን ሁሉ አስተዋጽዖ ማድረግ ሲሆን፤ ይህ አንዲሳካ የፕሮፌሰር አስተምህሮዎችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በተለይም ለወጣቱ ማዳረስ፣ ማሰረጽና በእወነትና በእውቀት ላይ በተመሠረተ ጥረት የበለፅገች፤ ከረሃብ፣ ከችጋር፣ ከድህነትና ከእርስ በእርስ ግጭት ነጻ የሆነች፣ ሰብዓዊ መብቶች የሚከበሩባት ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ነው።

የፋውንዴሽኑ ዓላማ (Mission)

የፋውንዴሽኑ ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 • ለሕግ የበላይነት፣ ለፍትሕና ለሰብዓዊ መብት መከበር አስተዋጽኦ ማድረግ፣

 • የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የምርምር ሥራዎች ተሰባስበው ለተመራማሪዎች ተደራሽ እንዲሆኑ የሚያስችል ማዕከል ማቋቋም፣

 • ያልታተሙና ታትመው በገበያ ላይ የሚገኙ ለማሳተምና ሌሎች ውጥን ላይ የነበሩ ፕሮጀክቶቻቸው ፍጻሜ እንዲያገኙ ማድረግ፣

 • በማኀበረሰብ ሳይንስ ዘርፍ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ርዕሶች ላይ ጥናት ለሚያደርጉ ተመራማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣

 • የግጥም ውድድሮችን ማዘጋጀት፣ ለአሸናፊዎች ማበረታቻ መስጠት፣ በሰብዓዊ መብቶች ሥራ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በፕሮፌሰር መሰፍን ወልደማርያም ስም ዓመታዊ ሽልማት ማበርከት፣

ለሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች መከበር ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ግለሰቦችና ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣

የተቋሙ ግቦች እና ግቦቹን ለማሳካት የሚከተለው ስልት (Objectives and Strategies)

የፋውንዴሽኑ ዓላማዎችና የማስፈጸሚያ ስልቶች የሚከተሉት ናቸው፤
 
 • ለሕግ የበላይነት፣ ለፍትሕና ለሰብዓዊ መብት መከበር አስተዋጽኦ ማድረግ፣
 • የፕሮፌሰር መስፍን የምርምርና የስነ ፅሑፍ ሥራዎች ተሰባስበዉ ለተማራማሪዎች ተደራሽ እንዲሆኑ የሚያስችል ማዕከል (ማዕከላትን)በአዲስ አበባና እንደ አስፈላጊነቱ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ማቋቋምና ማስተዳደር፣
 • ያልታተሙና ታትመው በገበያ ላይ የማይገኙ መፅሐፍትና የምርምር ስራዎቻቸውን ለማሳተምና ሌሎች ውጥን ላይ የነበሩ ፕሮጀክቶቻቸው ፍጻሜ እንዲያገኙ ማድረግ፣
 • በማኀበረሰብ ሳይንስ ዘርፍ ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ርዕሶች ላይ ጥናት ለሚያደርጉ ተመራማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ፣
 • የሥነ ፁሑፍ ውድድሮችን ማዘጋጀት፣ ለአሸናፊዎች ማበረታቻ መስጠት፣
 • የማህበሩን ዓላማዎች ለማራመድ የሚያግዙ የተለያዩ የውይይትና የሥነ ጥበብ መድረኮችን ማዘጋጀት፣
 • ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦች እና ድርጅቶች በፕሮፌሰር መሰፍን ወልደማርያም ስም ዓመታዊ ሽልማት ማበርከት፣
በሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ጥናትና ምርምር ለሚያደረጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች የገንዘብ፣ የሀሳብና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ፣